ሰው ዘር አመጣጥ በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ አብዛኛውን የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ትሸፍናለች።
የቅሪተ አካል ምርምር ማስረጃዎች እንደሚያስረዱት ከሆነ ከ Chororapithecus Abyssinicus ( 12-7 ሚሊዮን አመት በፊት የተገኘው ሰው መሳይ ጦጣ) ጀምሮ እስከ homo sapiens(ብልቱ ሰው) እየተባለ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን ትሸፍናለች። ይህም ማለት በአፋር ክልል ሆርቶ አካባቢ ከ 160,000 እድሜ እስካለው የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሂደት ማለት ነው።
በቅርቡ ከተገኙ ግኝቶች ደግሞ 4.4 ሚሊዮን አመት ያለው Ardipithecus kadaba እና ከ 3.3 ሚሊዮን አመት በፊት ኑራለች ተብሎ የሚገመተው የተሟላ ሰውነት ያላት ሰላም ይገኙባታል። በቅሪጸ አካል ግኝት በጣም ታዋቂ ሆነችውና ከተሟላ የሰውነት አካላ ጋር የተገኘችው ሉሲ በሳየንሳዊ አጠራሯ "Australopithecus Afarensis" ወይም ድንቅነሽ የሚል መጠሪያ የተሰጣት ከ3.2 ሚሊዮን አመት በፊት ጥኖር የነበረችውና በጊዜው በሁለት እግሮቿ መንቀሳቀስ የቻለች የሶስት ጫማ ርዝመት ያላት ናት።
ሉሲ የተገኘችው በአፋር ክልል ሃዳር በሚባል አካባቢ ነው። በአሁኑ ወቅት የሉሲን ምስል የያዘው ቅሪተ አካል በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም ውስጥ ለሁሉም ጎብኚዎች ክፍት ሁኖ ይገኛል። በአጠቃላይ የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ የሚጀምረው ከ Australopithecus ሲሆን በሂደትም ወደ ተቀየረ፡፡ Genus homo ሶስት የለውጥ ሂደቶች አሉት በቅደም ተከተልም እንዲህ እናስቀምጣቸዋለን።
- Homo habilse (2.4-1.8 ሚሊዮን አመት)
- Homo erectus ( ከ 1.4-1 ሚሊዮን አመት)
- Homo sapiens (ከ200,000 አመት በፊት)
የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1000 BC እስከ 1991 EC
ኢትዮጵያ በተደራጀ ሁኔታ ታሪኳ የሚጀምረው ከመጀመሪያው ሚሊኒየም ቅድመ ልደተ ክርሰቶስ ነው። በድወሮው ዘመን የግብጽ ፎርኦኖች ከፑንት ላንድ ጋር የንግድ ልውውጥ ሲያደርጉ ነበር። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት ፑንት ላንድ የሚባለው ኣካባቢ አሁኑ የኤርትራ ዳርቻዎች ወይም ሶማሌ ላንድ ነው።
የደአማት ስረወ መንግስት በ8ተኛው መቶ ክ/ዘመን መቀመጫውን የሐ የሚባል ቦታ አድርጎ እነደነበር ይታመናል ። ሁኖም ግን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መንግስትና የተማላ መረጃ የሚገኝለት ስረወ መንግስት በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ትግራይ ክልል ውስጥ የተመሰረተው አክሱም ስረወ መንግስት ነው።
የአክሱም ስረወ መንግስት ለመውደቅ ከመዳረጉ የተወሰኑ መቶ አመታት በፊት ስረወ መንግስቱ ከ አራተኛው ክ/ዘመን ክርስትና ሃይማኖት መምጣት ጀምሮ የተመሰረተና እንደ ኢሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 800 CE ተጽእኖ ፈጣሪ ሆነ ሃያል መንግስት ነበር። የአክሱም ስረወ መንግስት መቀጠል የቻለው ከ 4ተኛው መቶ ክ/ዘመን እስከ 6ተኛው መቶ ክ/ዘመን ነበር።
ማዕከሎቹን አክሱምና አንጎት አድርጎ ይንቀሳቀስ የነበረው የአክሱም ስረወ መንግስት ደቡባዊ ኤርትራ ፣ ትግራይ እና በኣሁኑ ጊዜ በአማራ ክልላዊ መንግስት የሚገኙት ላስታና አንጎት ዋነኛ የግዛት አካባቢዎች ነበሩ። እንደ የሃ አይነት ቀደምት ማዕከሎችም ለአክሱም ስልታኔ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የአክሱም ስረወ መንግስት መሪዎች ሰዋክን (በአሁኑ ጊዜ ሰሜናዊ ሱዳን አካባቢ የሚገኝ) ቀይ ባህርና በርበራን ( በአሁኑ ጊዜ ደቡባዊ ሶማሌ ላንድ) የሚገኙ ቦታዎችን በቁጥጥር ስራቸው አድርገዋል።
በተጨማሪም የአክሱም ነገስትታት በ 4ተኛው ክ/ዘመን በዘመናዊት ሱዳን በአባይ ሸለቆ ላይ የበላይነታቸውን በመያዝ የሜርዌ ግዛት ላይ ጥቃት በመክፈት ግዛቷን አውድመዋታል። በአረቦች በኩል የሚገኙትን የቀይ ባህር አካባቢዎችን፣ የቀይ ባህር ዳርቻዎችንና ዘመናዊት የመንን በግዛታቸው ስር አስገብተዋል። የአክሱም መሪዎች በአራተኛው ክ/ዘመን ወደ ክርስትና ሀይማኖትን ተቀብለዋል። በሰበተኛው ክ/ዘመን በኣረብ ባህረ ሰላቴ የተነሳው የእስልምና ሃይማኖት ለአክሱም ስረወ መንግስት መንኮታኮት ትልቅ ሚና ነበረው። ነብዩ ሙሀመድ በሞቱበት ወቅት (.A.D. 632) የኣብዛኛው የአረብ ባህረ ሰላጤና የቀይ ባህር ዳርቻዎች በእስልምና ሃይማኖት ስር ሆነዋል።
በፍጥነት እየተስፋፋ የሄደው የእስልምና ሃይማኖት የባይዛንታይን ግዛትንና የሳሳኒያን ግዛት በኢስላማዊ አገዛዝ ስር እንዲወድቁ አድርጓ የአክሱምና የኢስላም ግዛቶች ግንኙነት የጥላቻ አልነበረም። ይህም የሆነው ነብዩ ሙሀመድ የእስልምና ሃማኖትን በሚሰብኩበት ወቅት እሳቸውን ሲከተሉ የነበሩ መዕምናን ላይ የመካ ቁረይሾች ስጋት ሲያሳድሩባቸው ባልደረቦቻቸውን ወደ አክሱም (ሀበሻ) ምድር ልከው በአክሱም ንጉሰ ከለላ በማግኘታቸው ነው። በእስልምና ሃይማኖት አሰተምህሮት መሰረት ነብዩ ሙሀመድየአረብ ኢስላሞች ወደ ሀበሻን ጅሃድ እንዳይዘምቱ አውጀዋል።
በዚህም ምክንያት የአክሱም መንግስት በአረቦች ዝንድ ልክ አንደ ሳሳኒያን ግዛት፣ እንደ ባይዛንታይን ግዛት ግዛትን እንደ ቻይና ግዛት ጥልቅ ቦታ ሰጥተውት ኑረዋል።የኋላ ኋላ እየቀነሰ ቢሄድም በቀይ ባህር ወደቦች መካከል ከአረቦች ጋር የንግድ ልውውት ቀጥሎ ነበር። የአክሱም መንግስት የገቢ ማስገኛዎቹንና ለሃይሉ ወሳኝ የነበሩትን ደቡብ መእራብ አረብን፣ የቀይ ባህር ወደቦችንና የንግድ ቦታዎችን እያጣ መጣ። በኋላም ቀስ በቀስ ወሳኝ ከሆኑ የግዛቱ ቦታዎች በማፈግፈግ የግዛቱን አቅጣጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በማድረግ ወደ አገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ማስፋፋት ጀመረ። በመጨረሻ አካባቢም አክሱም የንጊሶች ንግስና ዘውድ መጫኛና የሃይማኖታዊ ማዕከል ቦታዎች ብቻ ሁና ቀጥላለች።
ደቡባዊ ትግራይ አገው ኣካቢ የሚገኙት ላስታ፣ ዋግና አንጎት እንዲሁም የኣማራ አካባቢዎች ላይ በአክሱም ሃማኖታዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ትውፊቶች ላይ ተጽዕኖ ፈጥረዋል። በሌላ በኩል የሴም ቋንቋዎች፣ የአክሱም እደ ጥበብና ባህላዊ ትውፊቶች የክርስትና ሃይማኖት ወደ ሀገሪቱ ደቡባዊ አቅጣጫ እንዲስፋፋ በማድረግ እረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
በአስረኛው ክ/ዘመን የዛግዌ ክርሰቲያናዊ ስረወ መንግሰት ተመሰረተ። የዛግዌ ስረወ መንግስት ልክ እንደ አክሱም ስረወ ምንግስት ሁሉ አብዘናውን የደቡባዊ ኤርትራ ደጋማ ቦታዎችን፣ ሸዋን፣ የአዶሊስ የወደብ ዳርቻንና በሶማሌ ላንድ የሚገኙትን ደቡባዊ ዘይላ አካባቢዎችን ተቆጣጥሯል። ነገር ግን የቀይ ባህር የንግድ ማዕከል በአረብ ከሌፌት ስር ሁኖ መቀጠል ችላል።
የዛግዌ ስረወ ምንግስት የት እንደተናሳና መች እንደጀመረ የሚያመለክት ግልጽ ሆነ መረጃ አልተገኘም። ነገር ግን በ 10 ኛው ክ/ዘመን መቀመጫ ማዕከሉን ሮሃ ወይም አዳፋ አድርጎ ነበር ተብሎ ይገመታል። ኣካቢውም ላሊበላ ተብሎ ይጠራል። ላሊበላ ስያሜውን ያገኘው 12 ውቅር አብተ ክርስቲያናትን ሰርቷል ተብሎ ከሚገመተው የዛግዌ ስረወ መንግስት ንጉስና የሃይማኖት መሪ ነበር።
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲናት በጣም አስደናቂና ለእይታ ማራኪ ናቸው። አብያተ ክርስቲያናቱ በዩኔስኮ (UNESCO) በአለም ቅርስነት ተመዝግበው ይገኛሉ። የመካከለኛው ዘመን የአውሮጳ ጽሐፊ ፓሪስተር ጆን ንጉሰ ላሊበላ ቅድሰት ምድር እየሩሳሌምን በማሰመለስ ስራ ላይ የመስቀል ጦረኞችን ሊረዳ ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ታላቅ የክርስቲያን መሪ አንደነበር ገልጿል።
በኋላም በ1270CE (Christian era) የአማራ መሳፍንት የሆኑት ዩኩኖ አምለክ የዛግዌን ሰረወ መንግስት መንግስት በማስወገድና ዘሩንም ከአክሱም መሪዎች ጀምሮ እስከ የእስራኤሉ ንጉስ ሰለሞን መሆኑን በማወጅ ራሱን አጼ ብሎ ሾመ፡፡ በዛን ዘመን የአፄ ዩክኖ አምላክን ስልጣን የሚያጠናክር ክብረ ነገስት የሚባል መጽሐፍ (ህግ) ተፃፈ፡፡ መፅሐፍ የአክሱም መሪዎች ዝርያቸው ከንግሰት ሳባና ከንጉስ ሰለሞን ከተወለደው አፄ ሚኒሊክ መሆኑን ይገልፃል፡፡ የዩኩና አምላክ መንገስ የሰላምናዊ አገዛዝን እንዳስመለሰ ይታመናል፡፡ የዘግዌ መሪዎችም ከንጉስ ሰለሞን ዘር ስላልመጡ ስልጣን አይገባቸውም ብሎ ያምናል ዩኩኖ አምላክ፡፡
የሸዋ አማራ ስረወ መንግስት (ከ13 እስከ 16ተኛው ክ/ዘመን) የመካከለኛው ዘመን የኢትዬጵያን ስልጣኔ ይወክላል፡፡ በዚህ ዘመን የክርስትና ሀይማኖች በአገሪቱ የተስፋፋበት፣ የእደ-ጥበብ ስልጣኔ ውጤቶች ያበቡትና ትግራይ ውስጥ ብዙ ቤተክርስቲያናት ከአለት የተገነቡት ዘመን ነበር፡፡
ኋላ ኋላ የመጀመሪያው የሸዋ አማራ ግዛት አስተዳደር ከደቡባዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የተነሱት ሀይለኛ የሙስሊም ስልጣኔዎች ፈተኑት፡፡ ከነዚህ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ሰሜን ምስራቅ ሸዋን የተቆጣጠረው የኢፋት ሱልጣኔትና ሀረርን ዋነኛ መቀመጫውን ያደረገው የአደል ሱልጣኔ ናቸው፡፡ በኋላም የአዳል ሱልጣኔት ቀይ ባህርንና ወደ እስልምና የገቡትን በአገሪቱ ምስራቅ አካባቢ የሚገኙትን አፋርና ሱማሌን በግዛቱ ስር አደረገ፡፡ በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙት ሌሎች ሥልጣኔዎች በክርስቲያን ግዛት አስተዳደር ግብር እየገበሩ የሚኖሩት የሀድያ፣ የባሌ የዳወሮ፣ የፈታጋር፣ በምዕራብ አቅጣጫ የዳሞት ስልጣኔዎችና ግዛቶች ናቸው። በ15ኛው ክ/ዘመን በክርስቲያን ግዛቶችና በአደል ሱልጣኔዎች መካከል የመናቆርና የጠብ ሁኔታ ተጀመረ። ነገር ግን በ16ኛው ክፍለ ዘመን የግዛቱን ማዕከል ሐረር ያደረገውና በኋላም 1520 ውጤታማ የጦር መሪ የሆነው ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል ገአዚ በቅጽል ስሙ ግራኝ አህመድ ተፈጠረ፡፡
ኢማም አህመድ (አህመድ ግራኝ) የክርስቲያን ግዛት ሀይልን ለመስበር ውጤታማ የተባለለትን ጃሀድ አውጆ፣ በኋላም በ1529 ብዙ ቦታዎችን ተቆጣጣሪ፡፡ ሰራዊቱም በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በመካከለኛው የኢትዮጵያ ዘመን የነበሩትንና የስልጣኔ መገለጫ የሆኑትን ህንፃዎች፣ ንዋየ ቅዱሳኖች፣ ባህላዊ ትውፊቶችና ቅርጻ ቅርጾች አውድሟል ተብሎ ይገመታል፡፡ በ1541 የፓርቱጋል ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ መድረሳቸውን ተከትሎ የአዲሱ ስልጣኔት መሪ ኢማር አህመድ ከኦቶማን ቱርክ ወታደራዊ እርዳታ ጠይቋል፡፡ ነገር ግን የፓርቹጋል ወታደሮች ቀድመው ደርሰው የገላውድዮስን ሀይል በመርዳት በ1543 በጣና ሀይቅ አካባቢ ኢማር አህመድ ተገደለ፡፡ የኣደል ስልጣኔትም ወደቀ፡፡ ነገር ግን የፓርቹጋሎች ዋነኛ ተልዕኮ የነበረው በህንድ ውቅጣኖስ የንግድ ማዕከሎች ላይ ያላቸውን የበላይነት ለማጠናከር ነበር፡፡ ፓርቹጋሎች ኢትዬጵያ ውስጥ ከገቡ በኋላ ኢትዮጵያ ከነበረችበት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት እምነት ወደ ሮማን ካቶልክ እምነት እንዲለወጡ የመስበክ ስራ ጀመሩ፡፡ ይህ ተግባራቸው ግን በአገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ደረጃ የደረሰ ግጭት አስከትለ፡፡ ጦርነቱም እስከ 1632 ቀጥሎ ነበር፡፡ የነበረው ግጭት ከደቡባዊ ኢትዮጵያ አቅጣጫ በኩል ለተከሰተው የኦሮሞ አርብቶ አደሮች መስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ከገናሌ ወንዝ በመነሳት ወደ ሰሜናዊ ባሌ እና ፍታጋር ላደረጉት መስፋፋት አጋዥ ካደጉት ምክንያቶች መካከል 1 በ1520 የተፈጠረው የክርስቲያን ግዛት መሪዎችና የአደል ሱልጣኔት መሪዎች ጦርነት እና የሲዳማ ኪንግደም መውደቅ ዋነኛዎቹ ናቸው፡፡ መጀመሪያ አካባቢ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ዘመቻቸው ለዘረፋ የነበረ ቢሆንም የተቀናቃኞቻቸውን ድክመት ከተመለከቱ በኋላ በመጫላ ጋዳ ጊዜ (1554-1562) በአረፉባቸው አካባቢዎች መስፈር ጀመሩ፡፡ከፍታጋር የመጫ ቱለማ ጎሳ በአገሪቱ ደቡባዊ፣ ምዕራባዊና ሰሜናዊ አቅጣጫ ለመስፋፋት ችሏል፡፡
ይህ ኦሮሞ መስፋፋት የአደል ሱልጣኔትን በ16ኛው ክ/ዘመን አፈራርሷል፡፡ ነገር ግን የሐረር ጀጎል ግንብ የሐረርን ግዛት ከኦሮሞ ጥቃት ታድጎታል፡፡ የኦሮሞ እንቅስቃሴ (OROMO Movement) ወደ ሰሜን በመዝለቅ አብዛኛውን የሸዋ ግዛት በመቆጣጠር ወሎ ድረስ ተስፋፍቷል፡፡ በአገሪቱ ምዕራባዊና ደቡብ ምዕራብ በኩልም የኦሮሞ እንቅስቃሴ ባደረገው መስፋፋት በኢናርያና በጎጀብ ወንዝ ከጠንካራው የከፋ ግዛት ታላቅ ተቃውሞ ገጥሞታል።
ሊሙ፣ጂማ (በወቅቱ ጠንካራ ግዛት የነበረ)፣ ኢናርያ፣ ጎማና ጉማ የሚባሉ ግዛቶች (Kingdoms) በ1800 በጊቤ አካባቢ ተመስርተዋል፡፡ የአሮሞ መስፋፋት እየተጠናከረ በመጣበት ወቅት እየተዳከመ የመጣው የሰሜኑ ሰረወ መንግሰት መቀመጫውን ጎንደር በማድረግ ፓለቲዊ እንቅስቃሴውን ጀመረ፡፡ ጎንደር የሰረው መንግስቱ የክረርስትና ሀይማኖት የእደጥበብና የባህል ማዕከል በመሆን ማገልገል ጀመረች፡፡ የኦሮሞ ስርዓት በወሎና በሸዋ አብቦ መሪዎቹም በጎንደር የፓለቲካ ስርዓት ንቁ ተሳታፊ በመሆን በመጨረሻው የ17ኛ ክ/ዘመን ሰፊ ግዛቶችን በስሩ ማድረግ ችሏል። በኋላ ኋላም አጼ ባካፋ ከኦሮሞ ጋር ጋብቻ ፈጽሟል። በ18ኛው ክ/ዘመን እና በ19ኛው ግማሽ ክ/ዘመን የየጁ አስተዳዳሪ የነበሩት የራስ አሊ ቤተሰቦች በዘመኑ ፓለቲካ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡
የአፄው ስርዓት እየተዳከመ ሲመጣ የአማራ፣ የትግራይ የኦሮሞ መሳፍንቶች ጎንደርን ለመቆጣጠር የእርስ በእርስ ጦርነት አካሂደዋል፡፡ በ1800 አካባቢ የተሾሙት አፄዎች በየግዛቱ በሚገኙ መሳፍንቶች ይታገዙ ነበር፡፡ የተለያዩ መሳፍንቶች ጎንደርን ለመቆጣጠር እያደረጉት የነበረው ትንቅንቅ በጠንካራው አፄ ቴድሮስ ማለቂያውን አግኝቷል፡፡ አፄ ቴድሮስ የእንግሊዝ እስረኞችን ለማስፈታት በመጡ የእንግሊዝ ሀይሎች ጋር ጦርነት አካሂደው በመሽነፋቸው ራሳቸውን ሰውተዋል፡፡ አፄ ቴድሮስ መሳፍንቶችን በቁጥጥር ስሩ በማስገባት የአፄውን ስርዓት አጋዛዝ ማስመለስ የቻሉ ጠንካራ መሪ ነበሩ። አፄ ዮሀንስ እ.ኤ.አ 1881 መህዲ ብሎ ስሙን ያወጀውን የሱዳን መሪ መሐመድ አህመድ ላይ አሸናፊ በሚባል ደረጃ ውጊያ ያካሄዱ ቢሆንም ከድርቡሾች ጋር ጦር በመተማ ላይ በተካሄደው ውጊያ የአፄ ዮሀንስ መገደልን ተከትሎ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ስልጣኑን ተረክበው ከዚያ በፊት ለበርካታ ክፍለ ዓመታት የኢትዮጵያ አካል ያልነበሩት አካባቢዎች ማለትም ወደ ምስራቅ፣ ደቡብና ምዕራብ ሸዋን ግዛታቸው ማስፋፋትን ጀመሩ፡፡
የዳግማዊ ሚኒሊክ መስፋፋት በአካባቢው ከአውሮፓ የቅኝ ሀይሎች ጋር ከዚያም በኋላም በ1896 አድዋ ላይ ከጣሊያን መሸነፍ ጋር በመገጣጠሙ አፄ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ የራሷ ድንበር ያላት አገር አድርገው መመስረት ችለዋል፡፡ አፄ ሚኒሊክ ምንም እንኳን በአድዋ ጦርነት በአሸናፊነት ቢወጡም ኤርትራን በቅኝ ስራ ያደረገችውን ጣሊያን ማባረርና ማስወጣት አልቻሉም፡፡ በ1889-1913 አዲስ አበባ ከተማን የቆረቆሩት አፄ ሚኒሊክ የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዘመናዊነትን ምዕራፍ ተከሉ፡፡ ከአፄ ሚኒሊክ ህልፈተ ህይወት በኋላ በጭራሹ ዙፋንነትን ይዘው የማያውቁትን የወሎ ሙስሊም ኦሮሞ አመራርና በአፄ ዮሀንስ አማካኝነት ክርስቲናን የተቀበሉትን የራስሚካኤል የወንድ ልጅና የአፄ ሚኒሊክ የሴት ልጅ ልጅ የሆኑት ልጅ እያሱ ዘፋንን ተረከቡ፡፡
ልጅ እያሱ በአብዛኛው በደጋማው የሚኖሩትንና ክርስቲያን የሆኑትን የአማራና የትግራይ ህዝቦችን ለቀቅ በማድረግ ራቅ ብለው ሲኖሩ የነበሩ የሙስሊም ኦሮሞችና ክርስቲያን ያልሆኑትን ህዝቦች ሕይወት ጎልቶ እንዲወጣ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡፡ እንደዲሁም ልጅ እያሱ ከአቶማኖችና ጀርመን ጋር ግንኙነት የፈጠሩ ሲሆን ከሁለቱ አገራት ጋር የተፈጠረው መቀራረብ ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ጋር በመገጣጠሙ እንግሊዝ ወደ ህንድ የሚወስደው የመንገድ መስመር በአቶማኖችና በጀርመን ቁጥጥር ስር ይወድቃል በሚል ስጋት ቁጣን ያስነሳባት ሲሆን ፈረንሳይ በበኩሏ ደግሞ የጂቡቲ ደህንነት ያሰሰበኛል በማለቷ በ1916 በሸዋ መኳንንት የተደራጀውን መፈንቅለ መንግስትን ደገፈ፡፡ በመሆኑም ልጅ እያሱ የአፄ ሚኒሊክ የሴት ልጅ በሆኑት ንግስት ዘውዲቱ የተተኩ ሲሆን ራስ ተፈሪ (ሀይለስላሴ) አማካሪና አልጋወራሽ ሆኖው ተሰየሙ፡፡
በ1930 የንግስት ዘውዲቱ ሕልፈተ - ሕይወት በኋላ አፄ ሀይለስላሴ የሚል ስም በመያዝ ራስ ተፈሪ ዙፋንን ጨበጡ፡፡ አፄ ሀይለስላሴ ከ1930-1974 ከአልጋወራሽነት ወደ አፄነት መሸጋገራቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አሀዳዊ አገዛዝን እንዲተከተል አደረጓት፡፡የንጉሱ አገዛዝ በ1935-1941 ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ ባካሄዳቸው ወረራ ሊቋረጥ ችሏል፡፡
ከእግሊዝ አማካሪዎች ጋር በመታገዝ በ1941 የኢትዮጵያ ላይ መወጣት ጋር ተያይዞ ብሪጣኒያ በ1948 ከኦጋዴን በመውጣት እስከ 1952 ኤርትራን መግዛትና መቆጣጠርን ቻለች፡፡ በዚህ ምክንያት አፄ ሀይለስላሴ ከሰሜን አሜሪካ ይበልጥ ብሪጣኒያን እነደሀያል አገር አድርገው መመልከት ጀምሩ፡፡ ስለሆነም በ1952 ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት አማካይነት ስትተዳደር ከቆየች በኋላ ከኢትዮጵያ ጋር መቀላቀሏን ተከትሎ አፄ ሀይለስላሴ በኤርትራ የነበሩ የህትመት ስራ፣ ንግድ፣ ማህበራት፣ የፓለቲካ ፓርቲዎችና የፓርላማ ተቋማትና አፈራር ሰው በ1952 ኤርትራ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገር እንዲትሆን አደረጉ ኣት፡፡ ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀሏን ተከትሎ የኤርትራ ህዝብ በኤርትራ ነፃነትና በኤርትራ ህዝባዊ ነፃነት ግንባሮች አማካይነት ለነፃነቱ መታገልን አቀጣጠለው፡፡ በግብጽና በሌሎች ‘አረብ ሀገራት በመታገዝ ሲደረግ የነበረው ይህ የኤርትራ የነፃነት ተጋድሎ በ1991 ዕውን ሲሆን በ1993 ኤርትራ በይፋ ነፃነቷን አወጀት፡፡ አፄ ሀይለስላሴ 1955 ህገመንግስትን በማርቀቅ ሀይል የሌለው ፓርላማን በማቋቋም በመሬት ፓሊሲ. በስልጣን ዕርከን ላይ እውነተኛ ማሻሻያና ማስተካከያ ሳያደርጉ ኢትዮጵያን እንድትዘምን አድርገዋል፡፡ በመሆኑም ሀገሪቷ በፊዳል ስርዓት ውስጥ እንድትቀጥልና በጥቂት የአማራ ፕሮክራሲ እንድትቆይ አደረጉ ኣት፡፡ ይህ ሁኔታ የህዝቦችን ተቃውሞ በተለይ በትግራይ በ1943 በኦሮሞና በሶማሊያ በ1960ዎች እንዲነሳ አደረገ፡፡
በወቅቱ አዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትና የተመድ ዋና መቀመጫ ለመሆን በቃች፡፡ እንዲሁም በሀይለስላሴ ጊዜ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጎን በመቆም በደቡብ ኮሪያ ቃኘ ተብሎ ሲጠራ የነበረውን ጦር ማዝመት ቻለች፡፡ የአፄ ሀይለስላሴ ስርዓት መራዘም፣ እያደገ የመጣውን የመሬት ቀውስ፣ ፍትሐዊ ያልሆነ የመሬት ክፍፍል፣ የልማት ዕጦትና በኤርትራ የሚካሄደው የአብየት ትግልን ያባባሰው ሲሆን በ1972 -1974 200,000 የሰው ሕይወት የቀጠፈው ድርቅና ረሀብ የአፄው ዕድሜ መግፋትና ለአልጋወራሽነት ሰው ያልተየመ መሆኑ ጋር ተጨምሮና የሰራዊቱን ክፍል፣ ተማሪዎችንና የ ሰራተኞችን ቁጣ አቀጣጠለው፡፡ በ1974 ወር ላይ ተከታታይ የሆነ የሰራዊትና የህዝብ የስራ ማቆምም ተከትሎ በሀገሪቱ የሰራዊት ሀይሎች ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ይህንኑ ይህ የተቋቋመው ኮሚቴ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ማስርና በሴፕተመበር ወር አፄ ሀይለስላሴን ገለል ከተደረጉ በኋላ የታሰሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ 60 ሰዎች በግፍ ተገደሉ፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ግልጽ ባልሆነ መንገድ አፄ ሀይለስላሴ ተገደሉ፡፡ ንጉሱ የሞቱት ግልጽ ባልሆነ መንገድ ነው የሚሉ ወገኖች ቢኖርም እሳቸው የሞቱት ተገድለው ነው የሚል ግምት ያመዝናል፡፡
1975 መጋቢት ወር ላይ የአፄው ስርዓት በይፋ ተወግዶ በምትኩ ግዛዊ የሰራዊት አስተዳደር ምክር ቤት ተቋቋመ፡፡ በ1974 ኢትዮጵያ ሲሺያሊስት አገር መሆኗን ታወጀ፡፡ ኢትዮጵያ ትቅደም በሚል መፈክር የአብዮታዊ የተሀድሶ ፕሮግራም ስራ ላይ ዋለ፡፡ የኢትዮጵያ ህብረተሰባዊነት ዓላማ የብሄራዊ ዴሞክራቲክ አብየት የሚያገለግል ሆኖ ተቀረፀ፡፡ በጥርና በየካቲት 1975 ደርግ ሁሉም ባንክ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና ዋና ዋና ኩባኒያችን የመንግስት እንደሆኑ ተወስነ፡፡
ሁሉም መሬትም በመንገስት ተወረሰ፡፡ በ1977 የካቲት ወር ላይ የደርግ ምክትል ሊቀመንበር ከሌኔል መንግስቱ ሀይለማርያም የመንግስት ግልበጣ በማድረግ ስልጣን ከጨበጠ በኋላ የሱን ተቀናቃኚዎችን በመግደል እኔ ፕሬዚዳንት ነኝ ብሎ ራሱን አወጀ፡፡ የቀይ ሽብር ተግባር መጀመሩን ተክትሎ የመንግስት የደህንነት ሀይሎች የተጠረጠሩት አባላትና የተቃዋሚ ሀይሎች ደጋፊዎች በማደን መግደሉን ተያያዙት፡፡ በአዲስ አበባበ ብቻ በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ በጅጉ የሚበልጡ ደግሞ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሞቱ፡፡ ይህ ሁኔታ አመፁን በተለይ በኤርትራና በትግራይ አቀጣጠለው፡፡
በ1977 አጋማሽ ላይ የኢትዮጵያ የውስጥ ሁኔታ መዳከሙን በማየት፣ የኢትዮጵያ ሶማሊ አከባቢና ሰፋ ያለ የሀገሪቷን ደቡባዊ ክፍለን ለመያዝ ሶማሊያ ኢትዮጵያን ወረረች፡፡
በ1978 የካቲት ወር ላይ በኩባ ወታደሮችና ከሶቨየት ህብረት በተገኘው ግዙፍ መሳሪያ በመታገዝ የሶማሊያ ሠራዊት ሳይሸነፍ በፊት የሀረር መግቢያ ላይ ደረሶ ነበር፡፡
የሶማሊያ ሠራዊት መሸነፍን ተከትሎ የደርግ ሰራዊት ወደ ኤርትራ እንዲቀሳቀስ ተደረገ፡፡ በወቅቱ ኤርትራ በኤርትራ ነፃነትና በኤርትራ ህዝቦች ግንባሮች አማካይነት ውጊያ ሲካሄድበት ነበር፡፡ የደርግ ሰራዊት ምንም እንኳን አብዛኛውን የኤርትራ ቦታዎችን ቢመልስም የኤርትራ የሁለቱን ነፃነት ግንባሮችን ማሸነፍ አልቻለም፡፡
እንዲሁም ደርግ ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ቢያዋቅርም ከትግራይና ከኦሮሞ የነፃነት ግንባሮች ተቃውሞ እየባሰበት መጣ፡፡ ደርግ ምንም እንኳን የሶቨየት ህብረት የፓለቲካና የወታደራዊ ዕገዛ ቢያገኝም የኤርትራ ህዝባዊ ነፃነት ግንባርን ጨምሮ የትግራይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባሮችን ተጋድሎ መደምሰስ አልቻለም፡፡
የደርግ የፓለቲካ ውድቀት ድርቅና ረሀብን አስከትለ፡፡ በተለይ በ1980ዎቹ አጋማሽ ላይ በድርቅና ረሀብ ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገደሉ አስቃቂ የሆነው የሰፈራ ፕሮግራም ዘመቻም ተስፋፋ፡፡
በ1980ዎቹ የሶቭየጽ ህብረት መክሰምን ተከትሎ ደርግ ከሶቭየት ህብረት ሲያገኘው የነበረ ድጋፍ ቆመ፡፡ ደርግ ተከታታይ የሆነ ከትግራይ የነፃነትና ከኢህአዴግ ግንባሮች ሽንፈት ሲደርስበት ከቆየ በኋላ በ1991 መንግስቱ ሀይለማርያም ወደዚምባቢዌ በመኮብለል እስካሁን ድረስ በዛው አገርየኖረ ይገኛል፡፡ በ2006ም መንግስቱ በዘር ማጥፋት ወንጀለና ሆኖ ስለተገኘ በሌለበት ፍርድ ተቆረጠበት፡፡ እንዲሁም ሌሎች የደርግ አመራር አባላት የሞት ቅጣት ፍርድ ተበየነባቸው፡፡ ምንም እንኳን የሞት ቅጣት የተከናወነባቸው የአመራር አባላት ዕውን ባይሆንም ከ20 ዓመታት እስራት በኋላ በ2011 ተለቀዋል፡፡
ኢህአዴግ ደርግ ከኮቦለለ ከአንድ ሳምንት በኋላ አዲስ አበባን በመቆጣጠር 17 ዓመት የፈጀውን አንባገነናዊውን የደርግ ስርዓት አስወገደ፡፡ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ 87 አባላት ያሉት የተወካዮች ምክር ቤትን በመመስረት የሽግግር መንግስትን አቋቋመ፡፡ የሽግግር ህገ መንግስቱም ለማቋቋም ብሄራዊ አርቃቂ ቻርተር ተቀመጠ፡፡
በ1992 ሰኔ ወር ላይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (OLF) በመንግሰት ውስጥ ያለኝ ድርሻ ስላስደሰተኝ በሚል ሳቢያ ከመንግስት በውጣት ወደ ትጥቅ መሳሪያ ትግል ተመለሰ፡፡ የኦሮሞ የነፃነት ግንባር ከመንግስት መውጣት ተገቢ ያልነበረ ቢሆንም ኤርትራን መቀመጫ በማድረግ መንግስትን የሚፃረር አነስተኛ እንቅስቃሴ ከማድረግ አልቀረም፡፡
በ1993 መጋቢት ወር ላይ የኢህአዴግ አጋር ፓርቲ ያልነበሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራቲክ ህብረት መንግስትን ጥሎ የወጣ ሲሆን የፌዴራላዊ ተቋሚ መንግስት መትክል ሂደት ግን በተሳካ ሁኔታ ቀጠለ፡፡ የፌዴራሊዝም ተቋም መመስረት ዓላማ ያልተማከለ ስልጣን ለቡዙሀኑ ብሄረሰቦች መስጠትና በፓለቲካ፣ ኢኮኖሚና ባህላዊ መስኮች ራሳቸውን እንዲያለሙ ነው ፡፡
በ1993 አዲስ ህገመንግስት የተረቀቀ ሲሆን አረቃቀቁም በ1994 ታህሳስ ወር ላይ በተመረጡ የህብ ተወካዮችና በ1995 ግንቦት ወር ላይ በተመረጠው ባርላማ ሰፊ ውይይት ከተደረገና ከፀደቀ በህዋላ ነው. በ1995 ነሐሴ ወር ላይ 9 ክልሎችንና ሁለት የቻርተር ከተሞችን በማካተት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ታወጀ፡፡ እወጃውን ተከትሎ በፓርላማ ውስጥ የአብላጫው ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ሟቹ መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖው የተመረጡ ሲሆን የቀድሞው የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዚዳንት ሆኑ፡፡ በ2000፣ 2005ና 2010 ብሔራዊና ፌዴራላዊ ምርጫዎች ተካሂደዋል፡፡
በኦክቶበር 2001 ወር ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጡ እንዲሁም በ2007 ላይም ኢህአዴግ መንግስት ሆኖ ከተመሰረተ ከአንድ ዓመት በኃላ ከአንድ መቶ የሚበልጡ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች ስራ ጀምረው መታየት ጀመሩ፡፡ ምንም እንኳን ወደ በኃላ እየቀነሰ ቢመጣም የግል ሚዲያ ቁጥር በስፋት ጨመረ፡፡
በ1994 ዓ.ም 547 የህዝብ ተወካዮች አባላት ምርጫ ተካሄደ፡፡ ይህ የህዝብ ተወካዮች ጉባዔ በ1994 ታህሳስ ወር ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና ህገ መንግስትን አረቀቀ፡፡ ዴሞክራሲያዊ ፓርላማ ተመስርቶ ህጋዊ በሆነ መንገድ ምርጫ ተካሂዶ ጠቅላይ ሚኒስተርም ተመረጡ፡፡ ህጋዊ ስልጣን በመንግስትና በሁለቱ ማለትም በህዝብ ተወካዮችና (547) በፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ከየክልሉ ምክር ቤቶች ተመርጠው የሚወከሉ ናቸው፡፡
በህዝብ ተወካዮችና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር የሚሾም ነፃ ፍርድ ቤት አለ፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ምክር ቤትና የእምባ ጠባቂ ጽ/ቤት አሉ፡፡ ህገ-መንግስቱ ክልሎች የራሳቸውን መንግስታትና ዴሞክራሲ እንዲመሰርቱ ሰፋ ያለ ስልጣን ይሰጣል፡፡ ይህ የተሰጠው ስልጣንም የፌዴራላዊ መንግሰት ህገ-መንገስትን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ክልሎች ህግ አውጪና ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤቶች ያላቸው ሲሆን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና ክልላዊ የዘርፍ ፅ/ቤቶችም አሏቸው፡፡ አንቀፅ 39 ክልሎች ከኢትዮጵያ የመንገጠል መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ የተመረጠ የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤቶች ከወረዳ ጀምሮ እስከ የቀበሌ አስተዳዳር ደረጃ የተዘረጋ ነው፡፡
በአዲሱ ህገ-መንግስት መሠረት በህዝብ የተመረጠ ብሔራዊ ፓርላማና የክልላዊ ህግ ማርቀቅ ምርጫ በ1995 ግንቦት ወር ላይ ነው የተካሄደው፡፡ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ በ2000 እንደተደረገው ምርጫውን አልተቀበሉትም፡፡ ይሁንና በ2005 በተካሄደው ምርጫ ላይ በአጠቃላይ ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል፡፡ የምርጫ ውጤቱም የ US ካርተር ማዕከል ታማኝነት ያለውና ውድድር ያንፀባረቀ በመሆኑ አዲስ የብዘሀ-ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓት ለመፍጠር እንደማዕዘን ድንጋይ የሚቆጠር ነው ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽንም ምንም እንኳን ሳያረጋግጥ የአንዳንድ የተቃዋሚ ሀሳቦችን ቢቀበልም 90% የምርጫው ሂደት ጥሩ ነበር የተካሄደው ሲልመስክሮ ኣል.የ መጨረሻ ምርጫ ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መቀመጫ (ወንበር) ከ12 ወደ 176 ከፍ እንዲል ተደረገ፡፡
ሆኖም ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተሰጠውን መቀመጫ ማሸነፍ አልቻሉም፡፡ ዋናው የተቃዋሚ ህብረት በመጀመሪያ ጥቅመት___________ወር ላይ ፓርላማው እንዲቋረጥ ጥሪ በማስተላለፍ ተከታታይ የአደባባይ ላይ አመፅ እንዲካሄድ አደረገ፡፡ መተካሄደው የ3 ቀናት አመፅ 7 ፖሊሲዎችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጋ ሰው ሞተ፡፡ የሞቱም ሁኔታ የፍርድ ቤት አጣሪ ኮሚቴ ያጣራው ሲሆን ፖሊስ አላስፈላጊ ሀይል ያልተጠቀመ መሆኖኑንም ግልፅ አደረገ፡፡
ለጊዜው በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተያዘ፡፡ ምንም እንኳን ከሁለት ዓመት በኃላ ቢለቀቁም አንዳንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ታሰሩ፡፡ የሁለተኛውና በ2010 የተካሄደው ምርጫ ቀድሞ ብጥብጥ እንዳይነሳ ለማድረግ አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ ፈረሙ፡፡ ሆኖም በውስጡ 8 ፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈው መድረክ የተባለው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ በ2005 በተካሄደው ምርጫ ላይ ፓርላማውን አቋርጦ ወጣ፡፡ በመድርክ አመራር ውስጥ ባለው ሽኩቻ ከ2010 ምርጫ በፊትም ይሁን በኃላ ኢህአዴግን ከመተቸትና በህዝቦች መካከል ጥላቻና ብጥብጥ እንዲነሳ ከማድረግ የዘለለ አማራጭ ፖሊሲዎችን ማምጣት አልቻለም .ከ2005 ምርጫ በኃላ ኢህአዴግ መዋቅሩን በማሻሻል የሴቶችና የወጣቶችን ድርጅቶችን እንዲስፋፋና ራሱንም በአገር አቀፍ ደረጃ ዳግም ጠንካራ በሆነ መሠረት ተደራጀ፡፡ በ2008 በተካሄደው አካባባዊ ምርጫ የአብላጫና የህዝብ ድምፅ በማግኘት ድልን ተቀዳጀ፡፡ ኢህአዴግ ይህ የተገኘውን ድል በማስቀጠል ትርጉም ባለው መልኩ የዕድገትና ልማት፣ መሠረተ-ልማት፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርትና ጤናን በስፋት በማሳካት ከ2005-2010 ባለው ግዜ ውስጥ የሁለት አሀዝ ዕድገትን ማምጣት ቻለ፡፡ ስለሆነም ምንም እንኳን 40% የአዲስ አባባ 499ኑም አሸንፎ የያዘ ሲሆን አጋር ፓርቲዎች ደግሞ 46 መቀመጫዎችን ያዙ፡፡ በ1991 ኢህአዴግ የውጭና የሀገር ውስጥ ፖሊሲዎችን አሻሻለ፡፡ የውጨው ፖሊሲና የብሔራዊ የሀገር ደህንነት ስትራቴጂው የሀገሪቱን ፈተናዎችና ህልውናዋን በመተንተን የተቀመጠ ሲሆን ፈተናዎቹም በምጣኔ ሐብት ወደ ኃላ መቅረት፣ ስፋት ያለው ድህነት፣ የዲሞክራሲ አስፈላጊነትና የመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ በሁሉም ደረጃዎች ዴሞክራሲ መዋቅርና ዲሞክራሲያዊ መንግስትን መዘርጋት የመትከል ናቸው ብሎ በግልፅ ለያቸው፡፡ ይህ ደግሞ በውስጣዊም ይሁን አካባባዊ የሰላምና የመረጋጋት ቁርጠኝነት ፍላጎትን ማስከተል አልቀረም፡፡ ስለሆነም ካለ ኤርትራ በስተቀር ኢትዮጵያ ከሁሉም የጎረቤት አገሮች የመልካም ግንኙነት ፍሬዎችን ማጨድ ከጀመረች ውላ አድራለች፡፡ አምባገነናዊ ደርግን ለመጣል ከኢህአዴግ ጋር ሲታገል የነበረው የኤርትራ ህዝባዊ ነፃነት ግንባር በ1991 ኤርትራን ነፃ በማውጣት በ1993 አገሪቷ ሠነፃ አገር መሆኗን በይፋ አወጀ፡፡